tirsdag 26. mai 2015

በኦሮሚያ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች ተገደሉ * “ምርጫ ሳይሆን ዘረፋ ነው የተካሄደው” – ዶ/ር መረራ ጉዲና

Gudina
 ትናንት እሁድ የተካሄደው ምርጫ በመሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ እንጂ ምርጫ አልነበረም ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ:: የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም የምርጫውን ሂደት አወገዙ::
ምርጫው በፌደራል ፖሊስ እና በልዩ ሃይሎች የሕዝብ ድምጽ እንዲሰረቅ መድረጉን ያጋለጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና በአምቦ አካባቢ የተቃዋሚ ፓርቲ 2 የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንም ለኢሳት ገልጸዋል:: ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በመንግስት ታጣቂዎች የምርጫ ኮሮጆ ከመሰረቁም በላይ በርካታ የምርጫ ታዛቢዎች መደብደባቸውና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል::
በአሪሲ ኮፈሌ እንዲሁም አምቦ ሚደጋን ቶላ ላይ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንና በሌሎች ላይም ጥቃት መፈጸሙን ዶ/ር መረራ ገልጸዋል:: ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ የተሰረቀውን ድምጹን ለማስመለስ እንዲታገልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar