fredag 15. mai 2015

በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ!


tegadelti



የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ:: በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል። በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar