የትኛውንም ታዛቢ ሆነ ማንኛውንም መራጭ የዘንድሮው ምርጫ እንዴት ነበር? ብላችሁ ብትጠይቁት እጅግ ሰላማዊ ነው ይላችኋል፡፡ በእይታ ደረጃ ትክክልም ነው፡፡ ቁም ነገሩ እርሱ አይደለም፡፡ የተሰራው ቀመር ላይ እንጂ፡፡ ኢህአዴግ አስከዛሬ ያካሄዳቸውን ምርጫዎች በሙሉ የጨረሳቸው በግርግረ፣በስርቆት፣ ሰውን በመደብደብ ብሎም በመግደል ጭምር ነው፡፡ ይህ ነገር የተነቃበት ኢህአዴግ ዘንድሮ ሌላ ዘዴ ዘይዶ መጥቷል፡፡ 1ለ5 የሚሉት ፍልስፍና፡፡
ኢህአዴግ በየጣቢያው ያስቀመጣቸው ታዛቢዎቹ አንድ አይነት ፎርም ይዘዋል፡፡ ያ ፎርም የሚያገለግለው 1ለ5ቹ የጠረነፏቻን ሰዎች ይዘው ሲመጡ ለመመዝገብ ነው፡፡ፎርሙ ላይ 4 ቋሚ መስመሮችና 1 አግዳሚ መስመር ያሰምሩበታል፡፡ ይህ ማለት 4 ተጠርናፊዎችና 1 ጠርናፊ መጥተዋል ማለት ነው፡፡ የሚገርመው ከዚህ መካከል 1 ተጠርናፊ ቢቀር እዚያው ውስጥ የኤክስ ምልክት ይደረግበታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምርጫ የቀረበው ወረቀት ሆነ ተብሎ እንዲያንስ ተደረጎአል፡፡ ይህም የተደረገው በተመረጡ ቦታዎች ላይ ሆነ ተብሎ ነው፡፡ ቆይ ማን ይሙት ምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የመራጭ ብዛት እያወቀ እንዴት ሆኖ ነው ወረቀት ሊያንስ የሚችለው፡፡ ህም ስህተት ሊመስል ይችላል፡፡ ኢህአዴግ ሆየ የተማረ ሰው እደማትወድ አኛ ብቻ ሳንሆን እራሳቸውም ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ስለሆነም ተምሮ መሰደድ የማይፈልገው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደማይመርጣቸው ስላዎቁ እጥረት የተከሰተ አስመስለው የአብዛኛው ያልተማረው መራጭ ቁጥር ከታወቀና አሸናፊነታቸውን ማታ ካዎቁ በኋላ ለተማሪዎቹ የመራጭነት ወረቀቱ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡ ሌላው ቁመራ ደግሞ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ የቀረበው እጅ ላይ የሚቀባው ቀለም በቀላሉ የሚለቅ መሆኑ ነው፡፡
በዚህም ምክንያት አንድ ሰፈር ውስጥ በተደረደሩት የምርጫ ጣቢያዎች ደጋፎዎቻቸው ተዟዙረው ካርድ አውጥተው ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲመርጡ የተሸረበ ሴራ ነው ፡፡ ልብ በሉ አንድ ሰፈር ውስጥ 4 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ ብለን ብንዎስድ መራጩ ሰው አንደኛው ላይ መታወቂያውን አሳይቶ ይመርጣል ሌሎቹ ላይ ግን ቀድሞ የተዘጋጀለትን የውሸት ስም እንዳስፈላጊነቱም በመደበኛ ስሙ ተጠቅሞ ሌላ ቦታ እንዲመርጥ ይደረጋል፡፡ ይህንን ሲያደርግ መታወቂያውም ሆነ የምርጫ ካርዱ ጠፋብኝ እንዲል ይደረጋል፡፡ ለማረጋገጥም የህዝብ ታዛቢዎች ሰውየውን ወይም ሴትየዋን ያውቋት እንደሆን ይጠየቃሉ እነሱም አዎ ይላሉ ስሙን/ስሟን ባያውቁ እንኩን እዚያ አካባቢ ነዋሪ መሆናቸውን ይመሰክራሉ፡፡
ስለሆነም መታወቂያም ሆነ የምርጫ ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ ይደረጋሉ፡፡ እኔ በነበርኩበት የምርጫ አካባቢ በ1 የምርጫ ጣቢያ ውስጥ ከ100-150 ሰዎች እነደዚህ ሲያደርጉ እነደነበር ተቀማጭ ታዛቢዎች አይሆንም ሲሉ የነዋሪ ታዛቢዎች ያውቋቸዋል እየተባለ ሲመርጡ እንደነበር ብዙዎቹ ነግረውኛል፡፡ይህንን ብዜት አዲስ አበባ ውስጥ ባሉት የምርጫ ጣቢያዎች ስታባዙት ምን ያህል ልዩነት እንደሚኖረው ለናንተ ትቸዋለሁ፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግ ሆዬ የዘንድሮውን ምርጫ ያለምንም ኮሽታ ጨረስኩት ብላን ቁጫ አለች፡፡ ድንቄም ኮሽታ የሌለበት ምርጫ!!!!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar