onsdag 20. mai 2015

ኢሕአዴጎች በጣም የሚያሣፍሩና የተንኮል ቡድን ነው - በየነ ጴጥሮስ (መድረክ)







ኢህአዴግና የሚመራው መንግሥት አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ፣ እንዲሁም የእስካሁኑ ሂደት አፈጻጸም ስኬታማ ነው ማለቱ “ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንቀት፣ ለኛም ዘለፋና ትምክህት ነው” ብለዋል የመድረክ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፡፡
ለምርጫ ቅስቀሳ ደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙት የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀመንበር ዶክተር በየነ ጴጥሮስ በገዥው ፓርቲ መግለጫ ላይ ለቪኦኤ አስተያታቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው ሲመልሱ “ኢሕአዴጎች በጣም የሚያሣፍሩና የተንኮል ቡድን ነው፤ በእነርሱ አባባል ኢሕአዴግ እንዲቆጣጠር አድርገናል ማለታቸው ነው” ብለዋል የመድረኩ መሪና ዕጩ ተወዳዳሪ፡፡
ዶ/ር በየነ አክለውም “ኢሕአዴጎች እየተክለፈለፉ፣ አይመርጠንም ያሉትንም እያስደበደቡ፣ እየደበደቡ፣ እሥር ቤት እያጎሩ፣ የምርጫ ታዛቢዎች ተብለው ከመድረክ ለምርጫ ቦርድ ተጠሪዎች ስማቸው የተሰጠን አንድ በአንድ እየለቀሙ እያሰሩ ናቸው፤ እየደበደቡ ናቸው፤ በገንዘብም እየገዙ ናቸው” ብለዋል፡፡
“እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት በኢትዮጵያዊነቴ የማፍርበትን ነው፤ - ያሉት ዶ/ር በየነ … የሚያደርጉትና የሚናገሩት የሰማይና የምድርን ያህል የተራራቀ ነው” ብለዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡http://amharic.voanews.com/content/beyene-petros-of-medrek-about-elections-2015-of-ethiopia-05-18-15/2776920.html

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar