በአፍሪካ ሀጉር ታሪክ ውስጥ አምባገነን መንግስታት በምርጫ ሥልጣን የማያስተላልፉበት እና የማይለቁበት ሁኔታ ነው ያለው። ይሁን እንጂ በ 1994 በጎረቤታችን ኬንያ አሁን ደግሞ በ 2007 በናይጂሪያ በተካሄደው ምርጫ የሕዝብ ድምፅ ያሽነፈበት እና ጨቆኖች ሥልጣናቸውን ለተከታዬቻቸው በሰላማዊ መንገድ ያስተላለፉበትን ለአብነት ያህል እንደ ምሳሌ ማንሳት ከተቻለ ነው እንጂ በተቀርው ግዚያት ግጭት የተስተናገደበት፣ የብዙሀንን ሕይውት መሰዋትነት ያስከፈለ እና የሚያስከፍል ነው የአፍሪካ ገዢ መንግስታትን የመተካቱ ተግባር። በኢትዬጵያ ገዥው አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሥልጣን ከተቆናጠጠበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ የአሁኑን የፊታችንን የግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጨምሮ በሀገሪቷ ውስጥ የይስሙላ ሀገር አቀፍ ምርጫ ሲካሄድ ይህ ለ 5ኛ ግዚ መሆኑ ነው። ይሁን እንጂ በነዚህ ባለፉት ግዚያት ውስጥ ለአንድ ግዚም ያህል ሰላማዊ፣ ፍታዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሄዶ አያውቅም። ከተካሄዱት ምርጫዋች አንፃር እና ከሀገሪቷ ተጨባጭ ተመክሮ በመነሳት የወያኔን መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይለወጣል ብሎ ማሰብ እጅግ ያስቸግራል። ይሁን እንጂ ላለፉት 24 ዓመታት በሞኖፖል በተቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሀን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት የሚጠብቅባት እና ፍትሀዊ ምርጫ እንደሚካሄድባት ሀገር አደርገው የገዢው ፓርቲ ፖለቲከኞች ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ሲደሰኩሩ ይደመጣሉ። ምንም እንኳን ሀገሪቷ በአንድ ፓርቲ መዳፍ ሥር ያለች እና ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚጣሱባት፣ ዜጎች እስር፣ ግድያ፣ ስደት እና መፍናቀል የቀን ተቀን ድርጊት መሆኑን ልቦናቸው የሚያውቀው ነገር እየሆነ ከሕዝብ ይልቅ የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ አካሎች ስለሆኑ የአስመሳይ ተግባራቸውን ገፍተውበት ይስተዋላሉ።
በመላ ሀገሪቷ ውስጥ በሽዎች የሚቆጠሩ ሕዝብ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ በሚታሰሩበት፣ በሚገደሉበት፣ በሚፈናቀሉበት፣ በሚሰደዱበት፣ በአደባባይ በሚሰቀሉበት እና ሀሳባቸውን እንኳን በነፃነት በማይገልፁበት፣ ከምርጫ ጋር በተገናኝ ብዙዎች ደብዛቸው በጠፋበት፣ ሲኦል በሆነበት ሀገር ውስጥ ሁኔታውን ሳያውቁት ቀርተው ሳይሆን አይደለም። በቅርቡ የአሜሪካ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዊንዲ ሽርማን “በሀገሪቷ የሚካሄደው ምርጫ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና የወያኔ መንግስትም በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተቋቋመ ነው” ያሉት መቼም ዲሞክራሲ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ምን እንደሆን ለሳቸው ማስረዳት የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ከሁሉም በላይ ችግሩን የሚያውቀው የችግሩ ሰለባ የሆነ ወይም የደረሰበት እና እየደረሰበት ያለው ሕዝብ ብቻ ነው። በመጀመሪያ ዲሞክራሲ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ምንድን ነው? ሕዝቦች መሪዎቻቸውን ነፃ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ወደ ስልጣን ማምጣት እና ማውረድ ሳይችሉ፤ ንቁ ተሳትፎ እንደ ዜጋ፣ ፖለቲካ ተቋም እና እንድ ሲቪክ ማህበራት ሳይኖር፤ የሁሉም ዜጎች ሰብአዊ መብት የተጠበቀ ሳይሆን፤ የሕግ የበላይነት እና ሕግ ለሁሉም እኩል ሳይያገለግል ነው ስለነዚህ አሳቦች የሚነሳው? በእርግጥ እነዚህ ከላይ የተገለጹት በወረቀት ላይ እንጂ ትክክለኛ በገቢርም ይሁን በተግባር በከፊልም ይሁን በሙሉ በሀገሪቷ ታሪክም ታይቶም፣ ተሰምቶም አይታወቅም። አምባገነኑ የወያኔ መንግስት የተቀናቃኝ እጩዎች ላይ የተለያየ ምክንያት በማቅረብ ከእጩነት በማግለል፣ አፈና፣ ዛቻ እና እስር በማድረስ፣ ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን፣ በሕግ እና በማዕቀብ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ በማድረግ፣ የብዙሀን መገናኛ በሞኖፖል በመያዝ እና ለግል የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ብቻ በመጠቀም፣ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳይመዘገቡ እና እንዳይወዳደሩ በማድረግ፣ በጉቦ እና በሌሎች ጥቅማ ጥቅም በመደለል የገዢውን ፓርቲ ብቻ እንዲመርጡ በማድረግ፣ ገለልተኝ የምርጫ ቦርድ በሌለበት፣ መራጩን ሕዝብ ገዢውን መንግስት የማትመርጡ ከሆነ አገልግሎት ማግኝት አትችሉም በሚባልበት እና በሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት እናደርሳለን ብሎ በሚስፈራሩበት፣ በሚዛትበት አምባገነን ሀገር እነዚህን የመሳሰሉ የገዢው ፖለቲካ ፓርቲ ማጭበርበሪያ መንገዶች እያሉ እንዴት ነው ፍታሀዊ፣ ግልፅ እና ሁሉንም ያሳተፈ ምርጫ ተካሄዶ በመሳሪያ ኃይል በሚያምን አምባገነን መንግስት ጋር ተወዳድሮ በሰላማዊ መንገድ መለወጥ የሚቻለው?
በከልለው ኡርጋ*
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar