onsdag 3. juni 2015

ኦነግ ‘አጠቃሁ’ አለ – ጃለኔ ገመዳ 03.06.2015

 በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮችና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ቅዳሜ፤ ግንቦት 22/2007 ዓ.ም የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ዘ ስታንዳርድ የሚባለው የኬንያ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ጋዜጣው በዌብሳይቱ ላይ ባወጣው ሪፖርት በግጭቱ መሃል አንድ ኬንያዊ የጥበቃ ሠራተኛ መገደላቸውንና የሞያሌ ሆስፒታልም ወረራ ተካሂዶበት እንደነበረ አመልክቷል፡፡
ሠራዊታቸው የሚዋጋው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን የገለፁት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ “… በመንግሥቱ ኃይሎች ላይ የኃይል እርምጃ ወስደናል…” ብለዋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar