ብሶት ወለደኝ ያሉት ሕወሃቶች “ከአሁን በኋላ ዴሞክራሲ ነው፣ መብት ይከበራል፤ በሕዝብ የተመረጠ መንግስት ነው ስልጣን ላይ የሚይዘው” ሲሉን ነበር። ሆኖም የሕወሃት መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ብሶትና ሰቆቃን በዜጎች ላይ እየፈጸመ ይገኛል። ኢትዮጵያዉያን ሕገ መንግስቱ በሚፈቅድላቸው መሰረት ሐሳባቸውን በመናገራቸው፣ “ሽብርተኛ” እየተባሉ በወህኒ እየማቀቁ ነው። እሥር ቤቶች ፣ እስረኞች የሚገረፉበትና ከፍተኛ ስቃይ የሚያገኙበት ቦታ ናቸው። ለአይምሮ የሚከብዱ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው። ፍርድ ቤቶች እንኳ ፍትህ ሊገኝባቸው፣ ካባ የለበሱ ደንቆሮና ሆድ አዳሪ ካድሬዎች ዳኛ ሆነው የሚቀመጡባቸው አሳፋሪና አሳዛኝ ተቋማት ናቸው።
በቅርቡ ኤዶም ካሳዬና ማህሌት ፋንታሁን በማእከላዊ እሥር ቤት የደረሰባቸውን፣ እንደ ኢትዮጵያዊ የሚያሳፍር እና አንገት የሚያስደፋ ሰይጣናዊ ድርጊቶችን አብዛኞቻችን አንብብነዋል። በእሥር ቤቶች ያሉ በሽተኞች የሆኑ፣ የአገዛዙ መርማሪዎችና ገራፊዎች፣ እነ ኤዶምን በጥፊ እየደበደቡ፣ ፣ ስብእናቸውንና ክብራቸው ገፈው፣ እህቶቻችን ራቁታቸውን ሆነው በፊት ለፊታቸው ጅምናስቲክ እንዲሰሩ ሲያስገድዷቸው ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ በሌሎች የዞን ዘጠኝ ብሎገሮች ላይም፣ ለመስማት የሚከበድና የሚሰቀጥጥ ድርጊቶች ተፈጸመዋል። ዞን ዘጠኞች የደረሰባቸውን ሁኔታ ፣ ማን እንዳደረሰባቸው በይፋ ህዝብ እንዲያወቀው ተደርጓል። የተለያዩ ሜዲያዎች ሁኔታውን ዘግበዋል። ባለስልጣናቱም ይሄን ጉዳይ እንዲያወቁት ተደርጓል።
ለአገርን ለሕዝብ የሚያስብ መንግስ፣ ስብእና የሚሰማው ባለስልጣን ቢኖር ኖሮ፣ እንዲህ አይነት ጨካኝ ተግባራት የሚፈጸሙ መርማሪዎች ከሃላፊነታቸው ተነስተው፣ ለፍርድ ቀርበው እንዲቀጡ ይደረግ ነበር። ሆኖም ያ አልታደረገም። ጭራሹኑ በ እስር ቤቶች ስቃዩ ጨመሯል። የኢትዪጵያ እሥር ቤቶ የናዚ ጀርመን እሥር ቤቶች እየሆኑ ነው።
መቶ አለቃ ጌታቸው ይባላሉ። አገር ዉስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባል ናቸው። ሽብርተኛ ተብለው ከሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዉይን ጋር ተከሰዋል። ወደ ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ጩኸታቸውን አሰሙ። የደረሰባቸው ግፍ ለማሳየት አካላዊ መረጃ ይሆን ዘንድ ልብሳቸውን አወለቁ። እግራቸው በቅጥቀጣ እንደተሰበረ የገለጹቶ መቶ አለቃ ጌታቸው፣ የዘር ፍሬያቸው በድብደባ እንደተኮላሸና መዉልደ እንደማይችሉ ገልጸዋል።
በሌላ ችልቶት የተሳሩ የመኢአድ ምክትል ፕሬዘንዳት አቶ ዘመነ ምህረትት ደግሞ ሌሎች ጓደኞቻቸውን ወክለው ሲናገሩ “ ትግሪኛ ካልተናገርክ ተብለን ራቁታችንን አድርገው ገርፈዉናል” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናገረዋል።

ሆኖም እነዚህ ጭራቆች ከልካይ የላቸውም። ፍርድ ቤትም ፣ ማንም እነዚህ ሰዎች ሊናገር የደፈረ የለም።
ይሄን ሁሉ ግፍና ጭካኔ ሲፈጽሙ እንዴት ከሃላፊነታቸው ሊነሱ አልቻሉም የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሱ ቀላል ነው የሚሆነው። ከበላይ ታዘው የሚያደርጉት ስለሆነ። ይሄም ችግሩ ያለው መርማሪዎቹ ላይ ብቻ ሳይሆን የሕወሃት አመራሮች ጋር እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይህ ዜጎችን የማሰር፣ የመደብደብ፣ ቶርቸር የማድረግና የማሰቃየት አሰራር በፖሊሲ ደረጃ ተግባራዊ እየሆነ ያለ የሕወሃት አሰራር ነው። ሠዎቹ ጨካኖችና ቂመኞች ናቸው። ሰዉን በማሰቃየት የሚደሰቱ ሰው ነን የሚሉ አዉሬዎች !!!!! ሰዎቹ፣ ይሄን ህዝብ እየረገጠን፣ እየገደልን፣ እያስፈራራን፣ እሸማቀቅን፣ እያዋከበን፣ እያፈናቀልን፣ ከሥራ እያባረርብ፣ እያስራብን፣ እየጨፈለቅን አደህይተን፣ አንገቱን አስደፍተን ፣ ፈርቶ አርፎ እንዲቀመጥ በማድረግ በጭካኔ ካልገዛነው፣ በስልጣን መቆየት አንችልም የሚል አስተሳሰብ ነው ያላቸው።፡ከሕዝቡ ጋር ተስማምቶ፣ የሕዝብን ጥያቄ አስተናግዶ፣ ነገሮችን ከማርገብ ዳግማዎ ግራዚያኒ መሆንን ነው የመረጡት። በሕዝቡ ላይ ጦርነት ማወጁን ነው የመረጡት። ምን ያህል እንደሚያዛልቃቸው በቅርቡ የሚያዩት ይመስለኛል።

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar