lørdag 12. oktober 2013

ትዝብት

Let me try to explain to you what a university student in Ethiopia has witnessed the work done of the weyane regim
It is as the following:- የዪኒቨርስቲ ተማሪዎች በነበርንበት ሰአት ስራ ልናገኝ የምንችለው አባል በመሆን ብቻም ሳይሆን በድፖርትመንት ህዋስ/እያንዳንዱን ድፖርትመንትና ባች መሰረት በማድረግ የሚደራጅ ሰብሳቢ፣ ፀሀፊና ገ/ያዥን ያካተተ አደረጃጀት/ ውስጥ ጥሩ ተሳትፍ በማድረግ በኢሀደጋዊ አስተሳሰብ ከታነፅን እንደሁም ይህ ተግባራችን ተቀባይነትን አግኝቶ ግሬድን መሰረት በማድረግ በሀላፊወቹ በኦርኔል ተሞልቶ መሰጠት እንዳለበት ተነገረን።
ብዙው ተማሪ እኔ ደሀ ነኝ የምማረው ደግሞ ስራ ይዠ በገንዘብ ራሴንና ቤተሰቤን ለመርዳት ነው ስለዚህ ተመርቄ ስራ የማላገኝ ከሆነ ድርጅቱን ባላምንበትም አባል መሆን አለብኝ እያለ ይገባል። ከዛም ወደ ላይብረሪ ከመሄድ ይልቅ ከዶርም ዶርም እየዞረ አባል የመመልመልና የስለላ ስራውን እያቀላጠፈ ያመሻል። በዩኒቨርስቲው ከሚሰጠው ኮርስ በበለጠ ሁኔታ በህዋስ ስብሰባ ተሳተፎ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በፈተና ውጤቱ C እና D ግሬድን በመሰብሰብ የሄደበትን አላማ ወደ ጎን በመተው የህዋሱን ግሬድ ግን A በማምጣት የመለስንና የአጫፋሪዎቹን ንግግሮች የሚደጋግም ፖሮት ይሆናል። ለዚህም ተግባሩ "A"," B ","C"ግሬድ የተጻፈበት ኦርኔል የሚባል የኢሀደግነት ምስክር ረቀት ይዘጋጅለታል።
የምረቃው ቀን በገበየነው እውቀት/ድንቄም እውቀት ገበያ/ መሰረት ሀገራችነን እና ህዝባችነን የተጀመረውን/ቆይ መጀመሩ ከሀያ አመት በላይ የፈጀው መተግበሩና መጨረሱ ስንት አመት ሊጨርስ ነው? /ልማት መልካም አስተዳደርና ድሞክራሲን መንግስት ባወጣው ፖሊሲና እስትራቴጂ መሰረት ከኢሀደግ ጎን በመቆም ለማስቀጠል ቃል እንገባለን በሚለው ኢሀደጋዊ ቡራኬ እንመረቃለን።
የሎሌነትና አጎንባሽነት፣ አስመሳይና የአድር ባይነትን፣ የግደለሺና የተስፋ ቢስነትን ማደንዘዣ ተወግተን እንወጣለን።
What do you say or what is your opinions about the suggestion to put down and ever barry the weyane regim trought our unity

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar