Hayu Kenate
አንድን ብዕር ለማቆም ብዙሃን ሲንጋጉ አይተናል፣ ይህ ታሪክ በዘመናት በአንዱ ዘመን ተብሎ የሚነገር ያለፈ ታሪክ አይደለም፣ ዛሬ በዚህ ዘመን የተከሰተ አስቂኝ ድራማ ነዉ እንጂ፣ ታድያ ርዕሱን ስትመለከቱ በቅጽበት እስክንድር ነጋን የምታስቡ ሰዎች ብዙ እንደ ሆናቹ አዉቃለዉ ፣ግን አይደለም ይህች የኦሮሞ ፎብያ ( Oromo Phobia) የሚባለዉን በሽታ የቀሰቀሰችዋ ብዕር ናት፣ አሁን ሁሉም ሰዉ ስለማን እንደማወራ የተረዳኝ ይመስለኛል። እስክንድር የታሰረዉ በራሱ ብዕር ሳይሆን ሌላ ሰዉ በማሳዉ ላይ የብዕሩን ቀለም እንዲዘራ በመፍቀዱ መሆኑን ደጋግመን ሰምተናል ። ይህንን ሲነግሩን የነበሩ የነፃነት ታጋይ ነን ባዮች ፣እነ ነፃነት ማተሚያ እና የመሳሰሉት የነፃነት ናፋቂዎች ፣ዛሬ በነፃ ሃገር ላይ የግለሰብን በነፃነት የመፃፍ መብት ሲያደናቅፉ ስናይ የመንግስታችን ድርጊት ብዙም አይገርመንም። መንግስታችን አይደለም በብዕር በንግግር ይደነብራል፣ ብዙዎች የዚህ ሰለባ ናቸዉ፣ እነ በቀለ ገርባ በተናገሩት ወርቅ በሆነዉ ንግግራችዉ ሊሸለሙ ሲገባቸዉ በእስር ይማቅቃሉ፣ ይህ የፈሪ ዱላ ለዓመታት ሚሊዮኖችን ሲያደማ የሺዎችን ነብስ ነጥቛል። ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ ካስፈለገ ከትላንት በስተያ በቀደምን ማስታወስ አያስፈልገንም፣ ትላንት የፈሰሰዉ የኢንጂነር ተስፋሁን ደም እስከ ዛሬ አልደረቀም እና ፣ታድያ ይህን ሁሉ ነገር ያነሳሁት ነፃነት ለጥቂቶች ብቻ በዘራቸዉ ልኬት ተሰፍሮ የሚታደል እንቁ በሆነበት ሃገራችን ዉስጥ፣ ነፃነት ስለ ተነፈገችው ብዕር ለማዉራት አይደለም ።. ዳሩ ግን የብዕር ነፃነት ቀለሙ እንደ ህንድ ዉቅያኖስ ፈሶ በሞላበት አለም ዉስጥ ፣ በነፃነት የምትቀዝፈዋን ብዕር ለማጥመድ ጎንበስ ቀና የምሉትን ሰዎች ድርጊት ስታስተዉል በድርጊታቸዉ ማዘንህ አይቀርም ፣ማዘን ብቻ አይደለም ዉሃ የማይቛጥረዉን እንቶ ፈንቶ ምክንያታቸዉን ስትሰማ ከጀርባ ያለዉ እኩይ አላማቸዉ ወለል ብሎ ይታይሃል ። • ነገሩ ወዲህ ነዉ በተስፋዬ ገብረአብ ተጽፎ በቅርቡ ታትሞ ገበያ ላይ ይዉላል በተባለዉ "የስደተኛው ማስታወሻ " ዉስጥ ስለ ተካተተዉ "የጫልቱ ሚደቅሳ " ታሪክ ሰምተን ለማንበብ ስንቋምጥ፣ ቀድመዉን ያነበቡ ሰዎች በጫልቱ ሚደቅሳ ታሪክ፣ በሽታቸዉ ተነስቶባቸዉ መቆሚያ መቀመጫ አጥተዉ በየድህረ ገጹ የሚያደርጉትን ስታይ ፣የቅርብ ጊዜ ትዉስታ የሆነዉን የጀዋር ላይ ሲካሄድ የነበረዉን ጦርነት ማስታወስህ ግድ ይሆናል ። ትላንትን እና ዛሬን አንድ ላይ አቆራኝተህ ፣አጠቃላይ ሁኔታዉን ስትገመግም፣ የእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ አለመቀየሩ ፣በሽታቸዉ በከፍተኛ ደረጃ ስር የሰደደ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ድርጊታቸዉ ለነገ አብሮነት ሳንካ መሆኑን ታያለህ ። ታዲያ ይህቺን አስተያይት ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር የአንዳንዶቹ አስተያየት መረን የለቀቀ ብቻ ሳይሆን አንባቢዉንም እንደ ሞኝ አድርጎ የሳለ ስለሚመስል ነዉ ። እስቲ አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕቢያ ሰላይ ነዉ ፣ብሎ ማዉራት ዛሬ ለምን አስፈለገ? ቢሆንስ ተስፋዬ የሰለለዉ ማንን ነዉ ? መቼ ? ይህን ዜና እየነገሩን ያሉት እነማን ናቸዉ ? ለምን ? ይህንን ጥያቄ ስታነሳ መልሱን ከራሱ ተስፋዬ ገብረአብ ፌስቡክ ገጽ ላይ ታገኘዋለህ እንዲህ ይላል "የስደተኛው ማስታወሻን ለማሳተም ከነፃነት አሳታሚ ጋር ውል ፈፅመን መፅሃፉ በህትመት ሂደት ላይ ነበር፡፤ በመካከሉ ግን መፅሃፉ ውስጥ ከተካተቱ ምዕራፋት መካከል ምዕራፍ 7 ተቆርጦ እንዲወጣ አሳታሚው ጠይቆኝ ነበር። የተጠየቅሁትን ማድረግ አልቻልኩም፡፤ " ማለቱን ካየን ታድያ ተቆርጦ እንዲወጣ የተጠየቀዉ ምእራፍ ስለ ኦሮሞ ህዝብ የያዘዉ ምዕራፍ መሆኑን ለመገመት ጠንቋይ መሆን አያስፈልግም ከዚህ በፊት ተስፋዬ “በቅርቡ ለንባብ በሚበቃው “የስደተኛው ማስታወሻ” በተባለው መፅሃፍ ላይ የኦሮሞን ህዝብ ነባር ባህላዊ ቅርሶች የሚነካካ በተለይም የቱለማ ገዳን በጨረፍታ የሚዳስስ አንድ ምእራፍ አካትቻለሁ። ርግጠኛ ነኝ የጫልቱ ሚደቅሳን ምእራፍ አንብባችሁ ስታበቁ መፅሃፉን አጥፋችሁ ታስቀምጡታላችሁ። ብዙ የተደበላለቀ አሳብም ወደ አእምሮአችሁ ይመጣል። “ያለዉን ማስታወስ በቂ ነዉ። ከዚህ ከተስፋዬ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ፣የተፃፉት አስተያየቶች አንዳንዶቹ አስቂኝ አንዳንዶቹ ደግሞ እጅግ አሳዛኝ ሆነዉ ታገኛቸዋለህ፡፤ 14 ገጽ የፃፉት ዳኛ ነኝ ባይ ችሎት ሳይቀመጡ ፍርድ ሲሰጡ ታያለህ ፣የፍርዳቸዉ ሰለባ ከሆኑት መሃል የሰዉ ለሰዉ ድራማ ላይ እንደ አስናቀ የሚሰራዉን አርቲስት አበበ ባልቻን እና በህይዎት የለሌዉንም ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔርን ታገኛቸዋለህ እስቲ ስለ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ቃል በቃል ያለዉን ላስነብባቹ "የቡርቃ ዝምታ ታትሞ እንደተሰራጨ ጠላቶችንም ወዳጆችም በብዛት አፈራሁ። የመጀመሪያውን አስተያየት የሰጡኝ ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ነበሩ። ማኪያቶ ጋብዘውኝ እንዲህ አሉኝ፣ “አሪፍ መጽሐፍ ጽፈሃል። አሪፍ መጽሐፍ ጽፌአለሁ ብለህ ካበጥክ ግን አለቀልህ። ገና አልጻፍኩም ብለህ አስብና ከዜሮ ጀምር። ሰዎች ሲያደንቁህ አትኩራራ። ሲያጥላሉህ ደግሞ አትደንግጥ። የሚረግሙህም የሚያደንቁህም ሰዎች በብዛት ይፈጠራሉ። መልስ እንዳትስጥ። ይህን እርሳውና ሌላ መጽሐፍ ጀምር። ይህች ደግሞ የፀጋዬ ገብረመድህን ዘዴ ናት . . .”
አይ ስብሃት! “አሪፍ መጽሐፍ ነው” አለ። እኔ ለነገሩ መንግሥቱ ኃይለማርያም በዓሉ ግርማን አላስገደለውም፣ ሊያስገድለውም አይችልም የሚወደው ጓደኛው ስለሆነ ያለ ጊዜ ነው የስብሃት አስተያየት የበቃኝ። እናም ምናልባትም ስብሃቱ መጽሐፉን አላነበበውም ወይም የመጽሐፉን ይዘት እና ውስጠ-ሴራውን በትክክል አልተረዳም፣ አለዚያም እንዳንዶቹ በኢትዮጵያ መፈራረስ ሴራ ውስጥ ዘው ብሎ ገብቶአል ማለት ነው። ብቻ ክፉ ቀን ጥሩ ነው። ወዳጅና ጠላትን ያስለያልና። " ታድያ እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ አንብበዉ በሰጡት የግል አስተያየታቸዉ በጠላትነት መፈረጃቸዉ አይግረማቹ ፣ዳኛዉ በሚቀጥለዉ ፍርዳቸዉ እንዲህ ይላሉ" አንድ ቀን የቴሌቪዥን ዜና ሳዳምጥ፣ የጎተራን ዲፖ ነዳጅ ሊያቃጥሉ ሲሉ የተደረሰባቸው የኦነግ አባላት ተያዙ በማለት የተወሰኑ ሰዎችን አሳዩን። ታውቃለህ በወቅቱ በልቤ ያልኩትን፣ እነዚህን የምን ፍርድ ቤት እንዳሉ ከነነፍሳቸው ማቃጠል እንጅ ነው ያልኩት። " ታዲያ በዳኝነት ደረጃ ለይ የነበረ ሰዉ አይደለም ፣ ተራዉም ሰዉ መንግስታችን የሚፈልጋቸዉን ሰዎች ለማሰር የዉሸት ድራማ እንደሚሰራ የማያዉቅ አይመስለኝም ። ዳሩ ግን ይህ ነዉ ፣ ያነዉ ማለት በዚህ ሰዉ ስራ ዉስጥ መግባት እዳይሆንብኝ ፍርዱን ለራሱ ትቻለዉ። ሌላዉ ዘ-ሀበሻ በሚባለዉ ድህረ ገጽ ላይ ተስፋዬን እና ይሁዳን የሚያወዳድረዉ ሰዉ ጽሁፍ በጣም ዘግናኝ ነዉ ። የተጠቀማቸዉን ቃላት ዳግም መጠቀም ራሱ ይሰቀጥጣል ፣ ስለዚህ በአንድ ወር ደሞዝህ እንኳን የሰዉን ልጅ የአይጥን ነፍስ እንኳን የሚያጠፋልህ ሞኝ አታገኝም ብለን ቀልደን ብናልፈዉ ይመረጣል። ከዚህ በተጨማሪ ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር፣ የቡርቃ ዝምታን ታሪክ ቁንፅል ሃሳብ፣ ስለተነካካ ይመስለኛል ፣የመጽሐፉ አንባቢዎች እጅግ በርክተዋል ይህ ጥሩ ነገር ነዉ በርቱ እያልኩ ፣የመጨረሻዉን ትዝብቴን ነግሬያችሁ አበቃለዉ፣ ሁለት ለደም የሚፈላለጉ አንጃዎች ተስፋዬ ላይ የአንድነት ግንባር መፍጠራቸዉ ነዉ። በቀደም የቡርቃ ዝምታን ሲፅፍ እነዚያ ቀለም ሲያቀብሉ እነዚህ ደግሞ ጥርሳቸዉን ሲነክሱበት እንደ ነበሩ ሰምተናል። ትናንት የጋዘጠኛዉን ማስታወሻ ሲፅፍ፣ እነዚህ ሲያጨበጭቡ ፣እነዚያ ደግሞ በጦር ሲያሳድዱት ነበር ፣ታድያ ዛሬ "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነዉ በሚባለዉ ቀለበት መጣመራቸዉን ሳይ፣ አብሮነታቹ የአብርሃም እና የሳራ ይሁንላቹ እያልኩ እሰናበታለዉ ደህና ሰንብቱ። ይህንን ጽፌ ትዝብቴን ለሰዉ ለማጋራት ኢንተርኔት ስከፍት የስደተኛው ማስታወሻ ተለጥፎ አየሁ በጣም ያሳዝናል የድካሙን ዋጋ ማግኘት ነበረበት ጠላቶቹ እንኳን ደስ አላቹ መጽሐፉ ግን እንደ ጉድ ይነበባል።
ሃዩ ቀናቴ

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar