አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 2፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በይግባኝ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ በማረሚያ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትናንት የአመክሮ ጊዜዋ ተጠናቆ ከእስር ተለቀቀች።
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ግለሰቧ በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሶስት የሽብር ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብላ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ ነበር።
በይግባኝ ባደረገችው ክርክር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኝነት ሙዋየዋን በመጠቀም የሽብር ቡድንን ደግፋለች በሚል ወንጀል ብቻ ጥፋተኛ ናት በማለት የ14 ዓመቱን ቅጣት ወደ 5 ዓመት ዝቅ አድርጎት እንደነበር የሚታወስ ነው።
በመሆኑም ግለሰቧ ትናንት የአመክሮ ጊዜዋ መጠናቀቁን ተከትሎ የእስር መፍቻ ተፅፎላት መለቀቋን ተረድተናል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar