በጂቱለሚ | Hagayyaa 5, 2014
ብዕሬን ስነጠቅ ፤ እሮሮዉ ሲበዛ ጠመንጃዉ ትዝ አለኝ::
መልዕክት ለትግራዩ የወንበዴ ቡድን!
እናቴ በተፈጥሮዋ ቻይና ርኅሩኅ ናት። ሰሞኑን ግን ከወትሮዋ በተለያ መልኩ ማልቀሱን አብዝተዋለች። እናቴ ‘Abdii koo’ በሚትለዋ አጭር ሀረግ ብቻ ደስታዋን ፣ ሀዘኗን ፣ ስስትዋን ፣ ጥልቅ የእናትነት ፍቅሯን ፣ ተስፋዋን ፣ ምክሯን ፣ ግሳፄዋን ፣ድካሟን ፣ ብርታቷን… ሁሉ ነገሯን ትገልጻለች። በቤት ዉስጥ የምንኖረዉ ሁለታችን ብቻ ነን ። ማታ ማታ እቤት ዉስጥ ቁጭ ስንል እኔ TVዉ ላይ ሳፈጥ እሷ ደግሞ በTVዉ ግርጌ በተንጠለጠሉ ፎቶዎች ላይ ዐይኗን ተክላ ታሰላስላለች። አንደኛዉ ፎቶ ያባቴ ሲሆን ሌሎቹ የዘመድአዝማድ ፎቶዎች ናቸዉ። እናቴ ከፎቶዎቹ መካከል አንደኛዉን አተኩራ ባየች ቁጥር ዕንባዋን መቆጣጠር ይሳናትና ወደ ጓዳ ገብታ ታለቅሳለች። ተመልሳ ትመጣና ደግሞ እንዳልከፋ ልታረሳሳኝ ትጥራለች።
እንዳለመታደል ሆኖ ይህንን የናቴን መሪር ህይዋትና በቤተሰቤ ላይ የተጫነዉን አስከፊ ግጽታ ማጤን የጀመርኩት ገና ሕጻን እያለሁ ነበር። አባቴ በከተማዋ ስመጥር የህክምና ባለሙያ ነበሩ። በአንድ የመንግስት ሆስፒታል ዉስጥ ከሚሰጡት የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ የግል ክሊኒክ ከፍተዉ በትርፍ ጊዜያቸዉ ለኀብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣሉ። አገልግሎታቸዉ ከሞላጎደል የነጻ ያህል ስለሆና አንዳንዴ የህክምና ቁሳቁስ መግዣ ወጪዎችን ከራሳቸዉ ኪስ ለመሸፈን ይገደዳሉ። እናም ቤተሰቡ ለክፉ ቀን እንኳ የሚሆን የመጠባበቂያ ገንዘብ የለዉም ነበር። ሆኖም ግን ቤተሰቡ በእጅጉ ደስተኛ ነዉ ማለት ይቻላል።
አባቴ ስለኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ፤ ባሕልና ወግ ያላቸዉ ጥልቅ ዕዉቀትና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደርሰዉን ብሔራዊ ጭቆናን አስመልክቶ ከሚያሳዩት ግልጽ ተቃዉሞ የተነሳ ወዳጅና ጠላት እንዲያፈሩ አስችሏቸዋል።በተለይ ደግሞ አንደበተርቱዕነታቸዉና አልበገሬነታቸዉ ታክሎበት የበርካታ ኦሮሞ ወጣቶችን ልብ በቀላሉ ማሸነፍ በመቻላቸዉ በጠላቶቻቸዉ ጥርስ ዉስጥ የመግባት ዕድላቸዉን አስፍቷል። በዚሁ አቋማቸዉ ሳቢያ በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትል ስለሚደረግባቸዉ የእናቴ የሰቀቀን ሕይወት መነሻው ከዚህ ይጀምራል።
አንድ ቀን አባቴ እንደ ልማዳቸዉ ሥራ ቦታ አምሽተዉ ወደ ቤታቸዉ በማምራት ላይ ሳሉ የቤተሰቡን ዓምድ የሚያናጋ ድርጊት ተፈጸመ። አባቴ በቤታቸዉ ደጃፍ ላይ በአምስት ጥይቶች ተደብድበዉ ተገደሉ። የቤተሰቡ ሕይወት በአጠቃላይ፤ የእናቴ ልብ ደግሞ በተለይ ላይድን ቆሰለ። በወቅቱ ሕጻን በመሆኔ የአባቴን መገደል ታሪካዊ አንምደታ በዉል ባልረዳም እንደጅረት የፈሰሰዉ ያ ደም በትንሿ ኣእምሮዬ በመቀረፁ እያደር የሕመሙ ጥልቀት ይሰማኝ ጀመረ።
ከአባቴ መገደል በኋላ በአካባቢዉ ላይ የተቀሰቀሰዉ ከፍተኛ የብሔርተኝነት ስሜት ከባዱን የቤተሰቤን ሃዘን በመጠኑም ቢሆን ያቃለለዉ ይመስለኛል። ለዓብነት ያህል አባቴ ጀምሮት የነበረዉ የመኖርያ ቤት ግንባታ ብሔርተኞቹ በቋቋሙት ግብረኃይል አማካይነት በሚያስገርም መልኩ ተጠናቅቆ ቤተሰቤ የዘመናዊ መኖርያ ቤት ባለቤት መሆን ቻለ። እናቴ እንደዋዛ የጀመረችዉ ትንሽዬ ሱቅ ግብረኃይሉ ባደራጀዉ የገበያ መዋቅር የቅድሚያ ተጠቃሚ እንድትሆን በመደረጉ በርካታ ደንበኞችን ኣፍርታ ወደ ዘመናዊ መደበር ተቀየረች። ትናንሽ ህጻናት እንኳ ሳይቀሩ ለዕቃ ግዥ ሲላኩ እረጅም መንገድ በማቋረጥ ምርጫቻውን የኛ ሱቅ ያደርጉ ነበር። እነሆ የአባቴ መገደል እንደ ገዳዮቹ ምኞትና ስሌት በአካባቢዉ ላይ የፍርሃትና መሸማቀቅ ስሜትን የሚያነግስ ሳይሆን በተቃራኒዉ የህዝቡን ቁጣና ብሔራዊ ስሜትን የሚያቀጣጥል ሆኖ ተገኘ።
እናም የተንኮላቸዉን መክሸፍ የተረዱ እኚህ የትግራይ ነፍሰገዳይ ወንበዴዎች እርር ድብን ኣሉ። በዚህ ዓይነቱ ሕዝባዊ ድጋፍ ከፍተኛ መጽናናት ያገኘችዉ እናቴ በሀዊ ለከፍተኛ ትምህርት ከቤተሰቡ ተነጥላ ርቃ መሄድ ምክንያት ተዳፍኖ የቆየዉ ኀዘኗና ስጋቷ ዳግም ተቀሰቀሰ።
ሀዊ ብቸኛ እህቴ ናት። በእኔና በሷ መካከል መጠነኛ የዕድሜ ልዩነት በመኖሩ የነገሮችን ትርጉምና አንድምታ ከኔ በተሻለ መልኩ በጥልቀት ለመረዳት ችላለች። በተለይ ደግሞ የአባቴን ገዳዮችና የግድያዉን ታሪካዊ ትርጉም ቀን በቀን ሳትሰላች ትነግረኝ ነበር። ሀዊ ብዙ ስሜቶችን ከአባታችን ወርሳለች። ከእሳቸዉ ህልፈት በኋላ ደግሞ በእልህና ቁጭት የእሳቸዉን ዓላማና አቋም ይዛ ወጣች። ልክ አባቴ ስያደርግ እንደነበር ባሕሏንና ታሪኳን በአደባባይ መመስከር ልማዷ ሆና። ድፍረቷ፣ ልበ-ሙሉነቷ፣ በራስ መተማመኗና ብሔራዊ ኩራቷ ላይ የሴትነት ዉበቷ ታክሎበት ያለዕድሜዋ ልዩ ግርማ-ሞገስና አድናቆትን ኣጎናጸፋት። ሀዊ በትምህርቷም ጎበዝ ከሚባሉ ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያዉን ስፍራ ስለሚትይዝ: በሁሉም ነገር ተምሳሌት ለመሆን የበቃች ብርቅዬ የማለዳ ጀምበር ሆነች።
በወርሃ ግንቦት 2014 እጅግ ሰቅጣጭ አደጋ በድጋሚ ወደ ቤታችን ገባ። ይህኛዉን አደጋ እኔም ሆንኩ እናቴ በፊፁም ልንቋቋመዉ የሚንችል ዓይነት አልሆነም። ሀዊ በምትማርበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ በነዚያዉ ልማደኛ ጭራቆች ተገድላ እሬሳዋ ተጭኖ መጣልን። ይህች የብዙሃን ተስፋ፣ የማለዳ ብርሃን በአጭሩ ተቀጨች። የማየዉና የምሰማዉ ነገር ሁሉ ክፉ ቅዠት እንጂ በዉኑ የማየዉ ክስተት አልመስል አለኝ። መፈጠሬን እስከምጠላ ድረስ ሁሉ ነገር ጨለመብኝ። ይባስ ብሎም ደግሞ እናቴ በድንጋጤ ብዛት ወደ ኣእምሮዋ መመለስ ተስኗታል። ይህንን የሰቀቀን ታሪክ ለመተረክ አሁንም ቢሆን አቅም ያንሰኛል።
እሮሮዉ በዛ፤ ግፉ ከልኩ አለፈ። ስቃዩ አንገሸገሸን። ከሀዊኮ ቀብር በኋላ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስቃይና መከራ ወደ ተፈራራቀብኝ ቄዬ ተመልሼ ብዙም የመቆየት ፍላጎት አልነበረኝም። ሆኖም ግን ለተወሰኑ ቀናት ከእናቴ አጠገብ መራቁን አልወደድኩም። እናቴ እነዚያን ፎቶዎች እያየች ሌተቀን አምርራ ማልቀሷን ቀጥላበታለች። መጽናናት ኣልተቻላትም። ከንግዲህወዲያእናቴንየሚያጽናናትነገርቢኖርአንድብቻነዉ።እሱምእነዚያንሰዉበላጭራቆችንአሳዶየሚወጋላትጀግናንአብዝታትሻለች። ያ ደግሞ ከኔዉ ከአንድ ልጇ ይጀምራል። መራራዉን የእናቴን ሀዘን ቁጭ ብዬ የማይበት ወቅት አለመሆኑን ተረዳሁ።
እናም አራቱንየቁርጥ ቀን ጓደኞቼን አስከትዬ ወደ በረሃው አመራን። የጀግና መሃላ ይዘን፣ የበረሃዉን ጥሪ ተከትለን በጀግኖች ዓምባ ፣ ዉሎዉና አዳሩ ከማይታወቅ ከባለ ጎፈሬዉ የበረሃ አንበሳ፣ ተራራና ሸለቆዉን ሲፈትሽ ዉሎ ከሚያድረዉ ከፈጣኑ በራሪ የደጋ ንስር ጋር ተቀላቅያለሁ። ወገቤ ከዝናሩ፣ ትከሻዬ ከብረቱ ጋር ተስማምቷል። የጥይቱ ቃቃታ ፣ የባሩዱ ሽታ ፣ የገዳዩ ፉከራ ተመችቶኛል። የወገኔን ደም ፣ የህዝቤን ዕምባ እስከምበቀልና የኦሮሚያን ነጻነት እስከማረጋግጥ ድረስ ፈጽሞ ዕረፍት ኣላገኝም። ለዚህ ደግሞ ቃሌ ፍጹም ፣ ትጥቄ ጥብቅ ፣ ሀሞቴ መራራ ፣ ክንዴ ብርቱ ፣ እርምጃዬ ፈጣን ፣ ዓላማዬ ጽኑ ነዉና ከእንግዲህ ይህ ነፍሰ-በላዉ የትግሬ ቡድንና ምስለኔዎቹ በየመንደሩና በየጎጡ እየዞሩ ኣሉባልታ እየነዙና ንጹሃንን እየገደሉ ተዳላድሎ የመኖሪያ ዘመን በእርግጠኝነት ያከትማል። አሁን ባላችሁበት ሁሉ ብሶት ከወለዳቸዉ ሕዝባዊ ታጋዮች ጋር ልትጋፈጡ ነዉ። ግፍና እሮሮዉ በዝቶ ሕዝባዊ እሳት ወልዷልና ለዘመነ ፍጻሜያችሁ ተሰናዱ።
የንጹሃን ደም ሁሌም ይፋረዳል!
ጂቱ ለሚ ነኝ ከኦሮሚያ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar