mandag 2. juni 2014

ያለመሰዋትነት የፈለጉት ግብ ላይ መድረስ አይቻልም!!!

አለማየው ግርማ
የኦሮሞ ህዝብ በየዘመናቱ አገሪቷን በመሯት ማለትም ገዥ መንግስት ሆነው ኢትዮጵያን በገዟት እና
ባስተዳደሯት ገዥዎች የተለያዩ ጭቆናና መከራ ቢደርስበተም ህዝቡ ለማንነቱ እና ለመብቱ ሲታገል የኖረ እና
እየታገለ ያለ ወደ ፊትም ነፃነቱ እና መብቱ እስኪከበር ድረስ የሚታገል ህዝብ ነው።

ይህ የሰሞኑም ጥያቄ ወይም ትግል የዚሁ ትገል አንዱ ገፃታ ነው። ከላይ እንዳነሳሁት በዚች አገር ውስጥ የኦሮሞ 
ህዝብ ላይ የተለያዩ ጭቆናዎች በደሎች ደርሰውበታል አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል። በዚህ በገዥው መንግስት 
ማለትም ከወያኔ አገዛዝ ጀምሮ እንኳ ብንመለከት በሃያ ሁለት ዓመት ውስጥ ከዚህ በፊት ከነበሩት ጨቋኝ 
ስርዓት እና አገዛዞች በተለየ እና በባሰ ሊባል በሚችል መልኩ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭቆናውና በደሉ ተስፋፍቶና 
ተባብሶ ቀጥሏል። ብዙዎች ያለምንም ምክንያት የኦሮሞ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ በግፍ በወያኔ ወታደሮች 
በጥይት ተደብድበው እየተገደሉ ነው። ከወያኔ ጥይት የተረፉት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻን ደግሞ 
ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ በአገዛዙ የተለያዩ ስሞች እየተለጠፈባቸው ወደ እስር እዲጋዙ እየተደረገና በእስር 
ቤትም ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። የሰሞኑም ድርጊት የዚሁ ማሳያ ነው። በርካቶችም 
ከስራቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፤ ሌሎቹም ገዳዩን የወያኔ አገዛዝ በመሸሽ በቅርብ እና እራቅ ወዳሉ አገራት 
እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል። በተሰደዱበትም አገር ተይዘውም ተላልፈው እየተሰጡ የአገዛዙ ሰለባ የሆኑም 
ጥቂቶች አይደሉም። በምስራቅ አፍሪካ አገራት በኬንያ ጅቡቲና መሰል አገራት የተፈፀመውን ማንሳት ይቻላል። 
በቅርቡ በአረብ አገራት በተለይም በሳውዲ አረቢያ በኦሮሞ ወገኖቻችን የደረሰውና እየደረሰ ያለው ሰቆቃ 
መቼውንም የምንረሳው አይደለም። ይህን ሁሉ በደል ግድያና እንግልት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰበት 
ያለውና አሁን አገሪቷን በጠበጃ ሃይል እና በጉልበት እየመራ ያለው የወያኔ አገዛዝ ነው።

አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ የሰሞኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ግድያ መነሻ የሆነው ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰ
ያለው ከመሬቱና ከንብረቱ ያለምክንያት በልማት ስም ከሚኖርበት ስፍራ ማፈናቀሉን በመቃወማቸው ብቻ
ነው። ይህ የማፈናቀል ተግባር እንዲ በይፋ ባይሆንም ከዚህ በፊት ሲፈፀምበት ኖሯል። በዚህ መፈናቀል ህዝብ
በንብረቱ የማዘዝና የፈለገውን የማድረግ መብቱ ተነፍጓል። ይባስ ብሎ በራሱ ንብረት ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ ተቀጥሮ
እና ተገዝቶ እንዲኖር በባህሉ እንዳይኖር በቋንቋው እንዳይጠቀም ተደርጓል። የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ሆኖ
በማንነቱ እንዳይታይ የባዕድን ማንነት እንዲወርስ እና እንዲኖር ተገዷል። አሁንም እየተገደደ ነው። እንግዲህ
ይህን ሁሉ ከላይ የጠቀስኳቸው ችግሮች ህዝባችን በወያኔ እስካሁን ሲፈጽሙበት ቆይቷል። ካሁን በኋላ ግን
የኦሮሞ ህዝብ በቃ በማለት በይፋ መሬቱን ሊቀራመተው የመጣውን ሃይል ለመቃወም መነሳት አለበት።
 በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ በተቃውሞ ትግል ላይ በወያኔ ወታደሮች በአደባባይ በጥይት ተደብድበው ህይወታቸውን
ላጡ ኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ ከልብ የተሰማኝን ሃዘን እገልጻለሁ። እንደዚህ የወያኔ አምባገነናዊነት
ማስፈራሪያና ጡጫ ሳይፈሩና ሳይበገራቸው በትግል ላይ ላሉ ወገኖች ትልቅ አክብሮት እና አድናቆት አለኝ። 


ትላንት ለኦሮም ህዝብ ነፃነት ሲሉ ብዙዎች እራሳቸውን ሰውተዋል። ይህ የሆነው ደግሞ ትግል መሰዋትነት 
ስለሚጠይቅና ያለትግል እና ያለመሰዋትነት ደግሞ የፈለጉት ግብ ላይ መድረስ ስለማይቻል ነው። የሰሞኑን 
የገዳዩን የወያኔ አገዛዝ ድርጊት በመቃወም በአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ ያለው የኦሮም ህዝብ ትግል 
በአጭሩ ስናየው አንድነቱን ያሳየበት ለወገኑ አለው ባይነቱን የገለጸበት ነበር ብል ማጋነን አይሆንም። በውስጥ 
ሆነው ከታገሉት ባልተናነሰ መልኩ በውጭ አገራት ያለውም የኦሮሞ ተወላጆች ለዚህ ትገል በግባር ቀደመትነት 
ወገንተኝነታቸውን አሳይተዋል። በተረፈ ይሄን በኦሮሞ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፤ በደል እና ሰቆቃ 
ችላ ብላችሁ ጥቅማችሁን አስበልጣችሁ ከዚህ አረመኔና ገዳይ መንግስት ጋር በተለያየ ጥቅም ተሳስራችሁ 
ያላችሁ የኦሮሞ ተወላጆች የታሪክ ተወቃሽ እንደምትሆኑ አትርሱ። ስለዚህ ይህ እንዳይሆን ሰፊው የኦሮሞ 
ህዝብ እያደረገ ያለውን የነፃነት ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ ወገናዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ዘለዓለማዊ ክብር ለተሰው ንጹሃን የኦሮሞ ተማሪዎች!!!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar