June 4, 2014
ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባል የጅባት እና ሜጫ ሰው በቶርች እንዲሞት ተደርጓል።
አምባገነኑ የሕወሓት ጁንታ ቢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች ላይ የሚያደርሰው አድገኛ የሆነ ዘረኝነትን ያዘለ የጥላቻ መከፋፈል እና እንዲሁም የተማሩ የኦሮሞ ወጣቶችን ለማጥፋት የሚደረገው ሩጫ እየተጋለጠበት መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነት እና የመብት እኩልነት ጥያቄዎችን የሚያነሱ ለሕወሃት አስጊ ናቸው ሕዝብን ይቀሰቅሳሉ ተብለው የሚፈሩ እና ከየመንገዱ እና ጎረቤት አገሮች ታፍነው የተወሰዱ የኦሮሞ ተወላጆች በትግራይ ክልል ውስጥ በከፍተኛ ጥበቃ በ እስር ቤት ስቃይ ላይ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቁጥራቸው 14 የሚሆኑ ታሳሪዎች የደረሱበት አይታወቅም ተብሎ ነገሩ ተደፋፍኖ ሕወሓት በከፍተኛ ደረጃ እያሰቃያቸው መሆኑ ታውቋል። ከ እስረኞቹ መካከል ከዚህ ቀደም ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባለ እና ከበጮ አከባቢ ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ በግርፋት እና በድብደባ ሕይወቱ እንዳለፈ ታውቋል። እንዲሁም እስር ቤቱ ውስጥ ከየመንገዱ ታፍነው የተወሰዱ የኢሕኣፓ የቀድሞ አባላት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ይህ በኢንዲህ እንዳለ በሰሜን ሸዋ አለባቸው ጫካ ውስጥ ሕወሓት ስድስት የኦሮሞ ተወላጆችን እንደረሸናቸው መርጃዎች አጋልተዋል። ወያኔ በተለያየ ጊዜያት ለኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከራከሩ እና ከጅቡቲ እና ኬንያ ታፍነው የመጡ እነዚህን 6 የኦሮሞ ተወላጆች ሰብስቦ በመውሰድ ከገደላቸው በኋላ በጅምላ እንደቀበራቸው ታውቋል። አለባቸው ጫካ ማለት የወያኔ እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች አንዱ ሲሆን በትግሉ ወቅት የተለያዩ የደርግ መኮንኖች እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚዎች እንደተረሸኑበት ይታወቃል። አሁንም በከፍተኛ ጥበቃ ብዛት ያላቸው ዜጎች ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል። ዚጎቻችን ደብዛቸው ጠፋ እንደወጡ አልተመለሱም ወዘተ እየተባለ በተለያየ ጊዜ ሮሮ ቢሰማም ምንም አይነት ፍንጮች እንዳልነበሩ ሲታወቅ በአሁን ሰአት ግን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያውያን ክየመንገዱ እና ጎረቤት አገር እየታፈኑ ካለፍርድ በምስጢራዊ ወህኒ ቤቶች እየተሰቃዩ እንደሆነ ተጋልጧል።
go to link ayyaantuu.com/horn-of-africa-news/
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar