ከአለማየው
ግርማ
ሰሞኑን በዓለማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማወዳደር ደረጃ የሚያወጣው 4
international colleges and universities (4 icu) የአፍሪካ ምርጥ የተባሉትን ዩኒቨርሲቲዎችን
ዝርዝር አውጥቶ ነበር። በእዚህ ተቋም ምርጫ መሰረት ወያኔ
ህወሃት የሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ መቶ ተመሳሳይ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አምሳ ሦስተኛ ደረጃ መያዙን
አሳውቋል።
አያሌ ምሁራን በትምህርት ጥራቱ ላይ አስተያየት ሲሰጡ አልሰማ ያለው የትምህርትን
ጥራትን በትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስፍኛለው የሚለው የገዥው መንግስት ፉከራ ከአፍ ያላለፈ ውሸት መሆኑን
አሳይቶናል።
ሌላው የሚገርመው ከተወሰነ
አመታት ወደ እዚህ በየክልሉ እንደ ተለጣፊ ሱቅ
የከፈታቸው ዩኒቨርሲቲዎች ለውድድር እንኳን አለመቅረባቸው ነው። ለነገሩ እንዴትስ ለውድድር ይቀርባሉ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ
እና ሃይል የሚማሩበት የአንድ ብሔር ተማሪዎች (የኦሮሞ ተማሪዎች) በሚጨቆኑበት የአስተማሪዎች ጥራት የሚለካው የድርጅቱ ማለትም የወያኔ ደጋፊ ወይም አባል በመሆን በሆነበት በአጭሩ
እነዚህን እና በርካታ ችግሮች ባሉበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ውጤት
መጠበቅ ከንቱ ነው። አወዳዳሪው ወይም መዛኙ እራሱ ወያኔ እስካልሆነ
ድረስ።
የአንድ አገር
እድገት ወይም የአንድ የአገር ለውጥ የሚመሰረተው በተማረው ሃይል እንደ ሆነ ይታወቃል ። የመብት ጥያቄም ከሚያነሳው
የህብረተሰብ ክፍል አንዱ የተማረው አካል ነው። ለዚህም ነው የወያኔ መንግስት የትምህርት ተቋሞችን ሙሉበሙሉ በቁጥጥር ስር
ያደረገው ከዚህ ህብረተሰብ የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን እንደሽብር ጠያቂዎችንም እንደ አሸባሪ የሚያየው።ከዚህም አንጻር ነው
የወያኔ አገዛዝ የመብትጥያቄ የሚያነሳውን የተማረ አካል በተለይ የኦሮሞን ተማሪዎች በመጨቆን ላይ ያለው።
አልፎም ተርፎም
የውጭ የትምህርት እድል ለዩኒቨርሲቲዎች ሲመጣ የህወሃት ካድሪዎች፤ የራሱን ዘርና የድርጅቱን ደጋፊዎች በመላክ የተቀረውን ተማሪ
ይሄንን እድል እንዳያገኙ ያደርጋል። የሚያሳዝነው ይህን ግፍ እና እንግልት ተቃቁመው እና እንደምንም
አልፈው ትምርታቸውን የጨረሱ ተመራቂዎች ስራ ለመቀጠር ሲሉ
የሚቀረበው የመጀመሪያ መስፈርት የህወሃት ደጋፊ ወይም አባል የመሆን
ጥያቄ ነው። ይሄንን ጥያቄ ጥቂቶች ከችግር አኳያ ሳይወዱ በግድ የድርጅቱ ደጋፊና አባል በመሆን ሲቀጠሩ ገሚሶቹ
ከአገራቸው እና ከቂያቸው ወደ ተለያዪ አፍሪካ አገራት የተሳካላቸውም
ወደ አደጉ አገራት ይሰደዳሉ። የተቀሩትም ወይም ያልተሳካላቸውም የመንገድ እራት ሆነው ይቀራሉ።
እንግዲህ ይህንን ሁሉ በደል በተማሪዎች በተለይ የኦሮም ተማሪዎች ላይ የሚፈፅመው
አባገነኑ የወያኔ መንግስት ነው። የትምህርትን ጥራትን በትምህርትቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስፍኛለው የሚለው የወያኔ አሉባልታ
ወሬ አይን ያወጣ ውሸት መሆኑን በ 4 international colleges and universities (4 icu) ተረጋግጧል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar