onsdag 10. august 2016
በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱ የኦሮሞ ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው አረመኔያዊ ግድያ የኢትዮጵያን የፖለቲካና የደህንነት ቀውስ በእጅጉ ያባብሳል።
ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄዱ የኦሮሞ ዜጎች ላይ የሕወሃት ስርዓት የፈጸመውን የጅምላ ግድያ በተመለከተ ከህዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የተሰጠ መግለጫ
pafdየኦሮሞ ህዝብ በሕወሃት በሚመራው ኣምባገነን ስርዓት ላይ እያካሄደ ያለው ተቃውሞ ከህዳር 12 ቀን 2016ዓም ኣንስቶ በቀጣይነት እየተካሄደ ይገኛል። የኦሮሞ ህዝብ በመላው ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እያካሄደ ነው። የሕወሃት መንግስት ዜጎች ላካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ የሰጠው ምላሽ ጥይት በማርከፍከፍ የጭካኔ ግድያ መፈጸም ሲሆን በዚህም እስከ ኣሁን ከ670 በላይ የኦሮሞ ዜግች ተገድለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል። ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በሚታወቁ እስር ቤቶችና ባልታወቁ ቦታዎች ታስረው ለቶርቸር ተጋልጠዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች ደግሞ ታፍነው ተሰውረዋል። ከተገደሉት ዜጎች መካከል ኣብዛኛዎቹ የዩኒቨርሲቲና የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ ወጣቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶችና ኣዛውንት ናቸው። የሕወሃት መንግስት ሃይሎች ይህንን የግድያ ወንጀል በህዝቡ ላይ የፈጸሙት በጎዳና ላይ ብቻ ሳይሆን በምሽት የህዝቡን መኖሪያ ቤቶች ሰብረው በመግባት ጭምር ነው። ኣያሌ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በወታደራዊ ካምፖች፣ ዜጎች በጅምላ በሚታጎሩባቸው ቦታዎችና ወደ ተለያዩ ያልታወቁ ስፍራዎች ተወስደው ታስረዋል። ተመሳሳይ ሁኔታዎች በቤኒሻንጉል፣ በኦጋዴን-ሶማሊ፣ በጋምቤላ፣ በኣማራ፣ በሲዳማ፣ በኮንሶ፣ በደቡብ-ኦሞና በተቀሩትም የሃገሪቷ ኣካባቢዎች በግልጽ እየታዩ ናቸው። የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ግንዛቤ እንዲጨበጥ ለማስቻልና የኢትዮጵያ መንግስት በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን እርምጃ በተመለከተ በስፋት ዘግበዋል። የኣውሮፓ ህብረትና የኣመሪካ የኮንግረስ ምክር ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱ የኦሮሞ ዜጎች ላይ በስፋት እየተፈጸመ ባለው ግድያ፣ እስራትና ሰቆቃ ያላቸውን “ስጋት” በመግለጽ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያና እንግልት እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች እያደረሰ ያለውን ስልታዊ መድልዖና ማግለል እንዲያቆም ጠይቀዋል።Ibsa Tumsa Ummatootaa Bilisummaa fi Dimokraasii – Hagayya 8 bara 2016 የህዝቦች ትብብር ለነጻነትና ለዲሞክራሲ መግለጫ — ነሃሴ 8 ቀን 2016ዓም
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar