ከአለማየው ግርማ
የኦሮሞ
ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ከአቶ
ሌንጮ ለታ አንደበት ሰማን እንዲ በሚል ቃል“ ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን” እሁን
ግን አቶ ሌንጮ ይሁኑ ድርጅታቸው አገር ቤት ገብተው
በመታገል እልማቸው እሁን ያደርጉ ይሆን? አይመስለኝም። የትኛውስ ድርጅት በአገር ውሰጥ በመሆን በመታገል
እደተሳካለትስ አቶ ሌንጮ ሳያቁት ቀርተው ነው። አልልም በአገር ውሰጥ በመሆን ይህንን አባገነናዊ የሆነውን ስርዓት ለመጣል በአገር ውስጥ በመሆን መታገል እንደማያዋጣ እና መቼም ቢሆን የአቁዋም ለውጥ እንደማያመጣ ከማንም በላይ ወያኔን ከእግር
እስከራሱ የሚያውቁት አቶ ሌንጮ ለታ ጠንቅቀው ያውቁታል። ከረሱትም ይሄንን ስርሃት እየታገሉ ካሉ ድርጅቶች መማር ይኖርባችዋል ባይ ነኝ።
ወያኔ ስልጣን ከመያዙም በፊትም እዲሆም ሰልጣን ከያዘ ቡሃላ በአገር ውስጥም ይሆን በውጭ አገራት የተመሰረቱ ድርጅቶች ይህንን ስርዓት
ማለትም አምባገነናዊውን የወያኔን ስርሃት እንጥላለን ብለው በአገር
ውስጥ በመገኘት ያደረጉት ትግል ሁሉ መና እንደቀረ ሁላችን የምናቀው እውነት ነው። ብዙዎቹ ፈርሰዋል ከመፍረስም ያልተናነሰ
ውሰጥም ያሉም አሉ ገሚሶቹም ይሄንን አባገነናዊ የወያኔን ስርዓት
ተቀላቅለው እየሰሩም ነው። በግልጽም ይሁን በስውር እንግዲ ይህ እውነት ከአቶ ሌንጮ ይሁን ከድርጅታቸው የተሰወረ እውነት ነው አልልም ።ታዲያ ይህ እውነት እያለ የእሳቸውም ይሁን የድርጅታቸው ራዕይ ወይም አላማ
ምን ይሆን? እሳቸው
እዳሉት ወደ አገር ገብቶ በመታገል አዲስ ታሪክ መስራት ወይስ ከትግል ማረፍ እሳቸው እዳሉት ወደ አገር ገብቶ በመታገል አዲስ
ታሪክ መስራት እንዳልሆነ እሙን ነው። እኔ ግን ከትግል እራስን ማግለል ይመሰለኛል። ተራ ንግግር ተናገርክ አትበሉኝ እንጂ ወደአገር
የሚያስገባቸው እውነት ቤተሰብ ወገን የተወለዱበት ቀዬ ናፍቆት ይመስለኛል።
ይሄም ከተናገሩት ቃል መረዳት ይቻላል። ለማንኛውም ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል የእኔ መልእክት ግን በህዝባችን በኦሮሞ ህዝብ መነገድ ይቁም እላለው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar